አነስተኛ የንግድ ስራ ጀማሪዎች ማወቅ ያለባቸው መሰረታዊ የኢትዮጵያ የግብር ህጎች 

ለአነስተኛ ቢዝነሶች ማወቅ ያለባችሁ አስፈላጊ የኢትዮጵያ የግብር ህጎች። ስለ ቫት ፣ የገቢ ግብር እና ሌሎች መሰረታዊያን።

በኢትዮጵያ ውስጥ አነስተኛ የንግድ ሥራ መጀመር ጥሩ ነው። ነገር ግን ያለ ትክክለኛ መረጃ የሀገሪቱን የግብር ስርዓት መረዳት ከባድ ሊሆን ይችላል።  ለአንድ ጀማሪ ነጋዴ የኢትዮጵያን መሰረታዊ የታክስ ህጎች ማወቅ እና መረዳት ብልህነት ነው። ምክንያቱም  ህጎችን ለማክበር፣ ቅጣቶችን ለማስወገድ እና ንግዱ እንዲሳለጥ ወሳኝ ሚና ስለሚጫወት ነው።.

ይህ ለአነስተኛ የንግድ ባለቤቶች ለሆኑ ወይም ለመሆን እያሰቡ ላሉት የተዘጋጀ ነው። በዚህ ጦማር የኢትዮጵያን የግብር ህጎች አስመልክቶ አስፈላጊ እና መሰረታዊ ነገሮችን ይዳስሳል። ለምሳሌ ሱቅ ለመክፈት፣ በአገልግሎት ላይ የተመሰረተ ኩባንያ ወይም የንግድ ሥራ  ለመጀመር ወይም ማነኝውም አይነት የንግድ ስራ ለመጀመር ያሰባችሁ ወይም ስራ ላይ ላላችሁ ይህ ጦማር መሰረታዊ የኢትዮጵያን የግብር ህጎችን ያሳውቃችሃል።  

ለምን ለአነስተኛ ንግዶች የኢትዮጵያ የታክስ ህግን ማወቅ አስፈላጊ ነው?

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2016 እና ሌሎች ደንቦች የሚመራው የኢትዮጵያ የታክስ ስርዓት የኢኮኖሚ እድገትን እያበረታታ የህዝብ አገልግሎቶችን ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው። ይህን ድጋፍ የሚሰጠው ደሞ ግብርን በመሰብሰብ ነው።  

ስለዚህ ለአነስተኛ ንግዶች የህግ ተገዢነት ለድርድር የማይቀርብ ነው። Tax law አለማክበር ቅጣትን፣ ህጋዊ አለመግባባቶችን ወይም የንግድ ሥራ መዘጋትን ሊያስከትል ይችላል። ከቅጣቶች ባሻገር የታክስ ህጎችን መረዳቱ ፋይናንስን ለማቀድ፣ ተቀናሾችን ለመጠየቅ እና ትርፍና ኪሳራን ባግባቡ ለማወቅ እና ለመጠቀም ይረዳል።

እያንዳንዱ አነስተኛ የንግድ ድርጅት ባለቤት ማወቅ ያለበት ቁልፍ የግብር አይነቶች። 

የኢትዮጵያ የግብር ሕጎች በጥቃቅን ንግዶች ላይ የተለያዩ የግብር ዓይነቶች ይጥላሉ። ማነኛውም የንግድ ድርጅት ባለቤት ማወቅ እና መረዳቱ በጣም አስፍላጊ ከሆኑት ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው ፡-

1. የንግድ ስራ ገቢ (Income Tax)

ማነኛውም ነጋዴ ወይም ግለሰብ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ካለው በእያንዳንዱ የግብር ዓመት በአዋጅ ቁጥር 979/2016 አንቀጽ 09 በተመለከተው ምጣኔ ወይም ምጣኔዎች መሠረት የንግድ ሥራ ገቢ ግብር እንዲከፍል ይደነግጋል፡፡ ታድያ እንደ አዋጁ በድርጅት ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የንግድ ሥራ ገቢ የግብር መጣኔ ሰላሳ በመቶ (30%) ነው፡፡  ነገር ግን ይህ ድንጋጌ ቢኖርም ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ግብር የሚከፍሉት እናም  በግለሰብ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት የንግድ ሥራ ገቢ ግብር መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

እንደ አንድ ትንሽ የንግድ ድርጅት ባለቤት ታክስ የሚከፈልበትን ገቢ በትክክል ለማስላት ገቢዎን እና የሚፈቀዱ ተቀናሾችን (ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ የመገልገያ እቃዎች፣ የሰራተኞች ደሞዝ) መከታተል ያስፈልጋል። ልክ ኩባንያዎች የኮርፖሬት ታክስ ተመላሾችን እንደሚያቀርቡት እናንተም በባለቤትነት ወይም በሽርክናዎች የግል የገቢ ግብር ተመላሾችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል ። ,.

2. ቫት ( VAT)

ቫት የታክስ አይነት ሲሆን እንደ መሰረታዊ የምግብ አይነቶችን ሳያካትት በሸቀጦች እና በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ 15% በመጨመር ከማህበረሰቡ የሚሰበሰብ የታክስ አይነት ነው።

አመታዊ የድርጅቱ ግብይት ከ ብር በላይ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን (ERA) መመዝገብ ግዴታ ነው። ስለዚህ ከሚሰጡ አገልግሎቶች ወይም ሽያጮች ላይ የቫት ደረሰኞችን መሰብሰብ እና ወርሃዊ ተመላሾችን ማስገባት ይጠበቅባችኋል። ይህ  ቅጣቶችን ለማስወገድ እና የግብር ተመኖን በትክክል ለማወቅ ጠቃሚ ነው።

3. የንብረት ግብር ታክስ (Property Tax)

ንግድዎ ንብረት ካለው ወይም ከተከራየ በንብረቱ አካባቢ እና ዋጋ ላይ በመመስረት የንብረት ግብር ሊተገበር ይችላል።

ለንግድ የተከራዩት ቦታዎችን አስመልክቶ ያለው ግብር አከራዮችን የሚመለከት ቢሆንም የኪራይ ውልዎን ሲፍጽሙ ግልጽ የሆኑ ነገሮች መስፈራቸውን ማረጋገጥ ያስፍልጋል ። ነገር ግን በባለቤትነት ላሉ ንብረቶች ዓመታዊውን የኪራይ ዋጋ እና እዳዎችን እንደሚተመን ማወቅ እና መዘጋጀት ያስፍልጋል። 

4. የተቀናሽ ግብር (Withholding Tax)

ይህ እንደ አንድ ጀማሪ የንግድ ድርጅት ባለቤት ማወቅ ካለባችሁ የግብር አይነት አንዱ ነው። ይህ የ ግብር አይነት የንግድ ድርጅቶ  ለአቅራቢዎች፣ ተቋራጮች ወይም አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ሽያጭ ሲፈጽም ከሚክፍሏቸው ክፍያዎች  ከ 2 እስከ 10 % እንደ ተቀናሽ ታክስ የመሰብሰብ ነው።  ይህንንም ሪፖርት ማድረግ እና ከገቢ ታክስ ላይ ተቋራጩ ማድረግ ይኖርባችኋል።

የንግድ ድርጅት ሲጀመር መከተል ያለባችሁ መሰረታዊ የግብር ግዴታዎች:

1. የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) መውሰድ 

ቲን የንግድዎ ልዩ መለያ ነው። ማነኝውም የስራ አይነት ይሁን ግብር የሚከፈልበት እስከሆነ ድረስ ቲን ማውጣት ግዴታ ነው። ስለዚህ   የንግድ ፍቃድ፣ መታወቂያ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ባቅራቢያ ባለ የገቢዎች ባለስልጣን ማውጣት ያስፈልጋል።  እናም የድርጅት የባንክ ሂሳቦችን ለመክፈት፣ ደረሰኞች ለማውጣት እና ተመላሽ ለማድረግ TIN አስፈላጊ እንደሆነም መገንዘብ ያስፈልጋል።



2. የፋይናንስ መዝገቦችን እና ፋይሎችን ማስቀመጥ 

ድርጅቶ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አይንት ገቢዎች፣ ወጪዎች እና ግብይቶች በፋይል አደራጅቶ መያዝ ያስፍልጋል። ገና ከጅማሮ እንደ ኤክሴል ያሉ አፕሊኬሽኖች መጠቀምን ማስለመድ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በ ህግ በተደነገገው መሰረት ለኦዲት ለመዘጋጀት  አንቮይሶችን፣ ደረሰኞችን እና የባንክ ስቴትመንቶችን ቢያንስ ለአምስት ዓመታት ማቆየት ያስፍልጋል።

3. ተማላሾች ን በግዜው መመለስ 

  • ወራዊ: የቫት ተምዝጋቢ ስትሆኑ ተመላሾችን በየወሩ በሚቀጥለው ወር የመጨረሻ ቀን ማስገባት አለባችሁ። 

  • አመታዊ: የገቢ ግብር ተመላሾችን እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማስገባት አለባችሁ።

ምክንያቱም ዘግይቶ ማስገባት ከታክስ ላይ ከ % ጀምሮ ቅጣቶችን ያስከትላል።

4. ታክስ ወድያውኑ መክፈል 

ያለባችሁን ታክስ ወድያው መክፈል ያስፈልጋል። ማቆየቱ ለ እንግልት እና ለቅጣት ያጋልጣል። እስከ % ቅጣት ሊኖር ይችላል። ይህ ብቻ ሳዮሆን ከ ገቢዎች ባለስልጣናት ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳይኖር ያደርጋል። 

ማጠቃለያ 

የኢትዮጵያ መሰረታዊ  የታክስ ህጎችን ማወቅ ማለትም የገቢ ታክስን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስን ፣ የንብረት ታክስን እና የተቀናሽ ታክስን መረዳት ብዙ ነገሮችን ያቃልላል።

 ስለዚህ የቲን ቁጥር መውሰድ፣ ፋይሎችን ማደራጀት ፣ተመላሾችን በግዜ መመለስ እና በግዜው ግብርን መክፍል እንደ አንድ አነስተኛ ድርጅት ትልቅ መሰረታዊ ስኬት ነው።  

ምንጭ፡ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2016፣ የኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን መመሪያ።